ዓማርኛ ኣከታተብ

Ethiopian Computers & Software
10145 E. 143rd Way
Brighton, Colorado 80602, USA
303-835-8025

ዓማርኛ ኣከታተብ

፩. በማውሱ ቀስት እስክሪኑ ላይ መጫን መክተብ ያስጀምራል።

፪. መርገጫዎችን ኣንዴ መጫን የሳድስ ፊደላትን ያስከትባል። ምሳሌ፦ ""tmhrt" "ትምህርት" ያስጽፋል። የላቲኑ መርገጫዎች ስሞች ከግዕዝ ፊደላት ድምጾች የቀረቡ ናቸው። የግዕዝ መርገጫዎች ሥዕል ከገጹ ታችኛው ግማሽ ላይ ይገኛል።

፫. የዓማርኛ መርገጫዎችን ለማየት "Help" ከእዚያ "Amharic Keystrokes" "ዓማርኛ መርገጫዎች" የሚለውን መምረጥ ያስፈልጋል። ገጹን ለመዝጋት ከላይ ቀኝ ማዕዘን የሚገኘውን "X" በቀስት መጫን ነው።

፬. የግዕዝ ቤት ፊደላትን ለመክተብ የ"Shift" ("ዝቅ") መርገጫን መርገጥ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ያህል "Shift h" "ሀ" ፊደልን ያስከትባል። ይህ የላቲኑን "H" የመርገጫ ስም እንደመክተብ ነው።

፭. የግዕዝ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ፡ ኣራተኛ፣ ኣምስተኛ፣ ስባተኛ እና ስምንተኛ ቤቶች የሚከተቡት በ"u". "i", "a", "e", "o" እና "\" በመጠቀም ነው። ምሳሌ፦ "ሁ" በ"hu"፣ "ሂ" በ"hi"፣ "ሃ" በ"ha"፣ "ሄ" በ"he"፣ "ሆ" በ"ho"`እና "ኋ" በ"]\" ይከተባሉ።

፮. ኣምስት እንዚራን ብቻ ያላቸው የግዕዝ ፊደላት የሚከተቡት በምልክት መርገጫዎች ነው። "ምሳሌ፦ "q/", "q[", "q\", "q;" እና "q]" እደተራው "ቈ"፣ "ቊ"፣ "ቋ"፣ "ቌ" እና "ቍ"ን ያስከትባሉ።

፯. የግዕዝ ምልክቶች "፡"፣ "፣"፣ "።"፣ ወዘተ... የሚከተቡት በ"Shift" ወይም "ዝቅ" እና 1፣ 2፣ 3፣ ወዘተ... ነው።

፰. የግዕዝ ኣኃዞች "፩"፣ "፪"፣ "፫"፣ ወዘተ... የሚከተቡት በ"ነጥብ" ወይም "Period" እና 1፣ 2፣ 3፣ ወዘተ... ነው።

፱. ኣኃዞች "፲"፣ "፳"፣ "፴"፣ ወዘተ... በ"ኮማ" ወይም "Comma" እና 1፣ 2፣ 3፣ ወዘተ.... ነው።

፲. በኣንድ መርገጫ የሚከተቡት በሚከተላቸው ዋየል እንዳይለወጡ የባለቤትነትን መርገጫ መጠቀም ያስፈልግ ይሆናል። ምሳሌ "u apostrophe" "ሥ" ያስከትባል፤ ኣለበለዚያ "uu" በጊዜው ገደብ ከተከተበ "ሡ" ያስጽፋል።.

፲፩. ግዕዝ ውስጥ የላቲን ፊደላትን ለመቀላቀል "Alphabets" የሚለውን ተጭኖ "Latin" ወይም "ላቲን" የሚለውን መምረጥ ነው። ኣንዳንዱን የላቲን ምልክቶች መርገጫዎች ሁለቴ በመምታት ላቲኑን መክተብ ይቻላል። ምሳሌ "ኮማ ኮማ" Comma Comma" የላቲኑን ኮማ "Comma". ሲያስከትብ "ኮማ መቀነስ" "Comma Minus" "ያንሳል" ምልክትን ማለትም "<" ፣ እንዲሁም "Tilde 2" "በ" ወይም "@" ያስከትባል።

፲፪. ኣንድን ጽሑፍ ለማባዛት የሚፈለገውን ማቅለም ወይም "Edit" መጫንና "ሁሉንም መምረጥ" ወይም "Select All" እና ከእዚያ "ቅዳ" ወይም "Copy" መምረጥ ያስፈልጋል። ወደ ሌላ ቦታ ለመገልበጥና ለመለጠፍ ለምሳሌ ወደ ኖትፓድ "Notepad" ለመውሰድ ኖትፓድን ከፍቶ እዚያ መለጠፍ ይጠቅማል። ኖትፓድን ለማግኘት "Start" ከእዚያ "Programs"፣ "Accessories" እና "Notepad" በመሄድ ኣዲስ ገጽ መክፈትና "Untitled Notepad ገጽ ላይ ጽሑፉን መለጠፍ ነው። ጽሑፉን ለመለጠፍ ወይም ለማስቀመጥ በቀኝ የማውስ ቀስት ገጹ ላይ መጫናን "Paste" የሚለውን መምረጥ ወይም የኖትፓድን "Edit" እና "Paste" መምርጥ ነው። ጽሑፉን ማስቀመጥ (ወይም "Save") እንዲቻል ግን "UTF-8" በሚባለው የመዝገብ ዓይነት መቀመጥ ኣለበት። ይኸን ለማድረግ "File" ከእዚያ "Save" የሚለው ስር "Encoding" ከሚለው "UTF-8" በተደፋው ማጣቀሻ መምረጥ ነው።

፲፫. ጽሑፉ ተከትቦ ካለቀ በኋላ ማስቀመጥ ወይም ኮፒ ተደርጎ ወደ ኢ-ሜይል፣ ማይክሮሶፍት ወርድ፣ ማይክሮሶፍት ወርክስ የመሳስሉት ፕሮግራሞች መለጠፍ ይቻላል። በጽሑፍ ምትክ ሳጥን የሚመስሉ ከታዩ ግን ኣንዱን ነፃ የዩኒኮድ ፒሲ ወይም ማክ ፊደል ከድረ ዓለም ወደ ኮምፕዩተሩ ማስገባት ያስፈልግ ይሆናል።

፲፬. ኣንድ የተከተበን ጽሑፍ ግድፈት ወይም ስህተት ለማረም ገጹን ኮፒ ኣድርጎ የነፃው ግዕዝኤዲት ገጽ ላይ መለጠፍ ነው። ለምሳሌ ያህል እዚህ Q and A with Dr Aberra Molla in Amharic ድረገጽ ያለውን ከፍቶ በማቅለምና ከተቀዳ በኋላ ግዕዝዜዲት ገጽ ላይ ኣምጥቶ በቀኝ የማውስ ቀስት "paste" በማድረግ መለጠፍ ይቻላል።

፲፭. ጊዜና ጣቶቻችሁን ከማያስፈልግ ድካም ከማትረፍ ሌላ ከኣሁን ወዲያ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም ከሦስት እስከ ስድስት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ ኣያስፈልግም።

፲፮. የነፃው ግዕዝኤዲት ገጽ ጥቅም ኢትዮጵያውያንና የግዕዝ ተጠቃሚዎች በነፃ የመላው ዓለም ድር ላይ ዊንዶውስና ማክ ውስጥ በአማርኛ እንዲከትቡ ነው። ለወደፊቱ ሌሎች ፊደላትን መጨመር ኣቅደናል። ሶፍትዌሩን ኮምፕዩተራቸው ላይ ለግል ጥቅም የሚፈልጉ ግን የተራቀቀውንና ኃይለኛውን ግዕዝኤዲት ቅጽ ፪ እንዲገዙ እናበረታታለን። ይህ የባለቤትነት መብቱ ሊሰጥ እየተጠበቀ በኣለ (ፓተንት ፔንዲንግ) ቴክኖሎጂ የተቀነባበረ ኣዲስ ፈጠራ በተለያዩ የግዕዝ ፊደላት ተጠቃሚ ቋንቋዎች በዩኒኮድ ፊደላት የሚጠቀሙ ፕሮግራሞች ውስጥ በእዚሁ ኣከታተብ ያሠራል። እንዲገዙ ስለምንፈልግ "Order" ከእዚያ "Order GeezEdit" "ግዕዝኤዲትን ለመግዛት" የሚለውን መጫን ያስፈልጋል። ሌላው ምርጫ የሚከተለውን ኣጓዳኝ http://www.geezedit.com መጠቀም ነው።

 
 
error: Content is protected !!